QIYAS በኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

የ4 ወር የቅያስ – ክህሎት ለሥራ (QIYAS – Skills for Job) – ግራፊክስ ዲዛይን ስልጠና ለተመራቂ ተማሪዎች እና ስራ ፈላጊ ወጣቶች በ Entrepreneurship Development Institute (EDI) – Ethiopia የሚመራ በMohas Consult ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ልማት ማጎልበትና የስራ ፈጠራ ማዕከል ጋር በመተባበር እየተሰጠ ይገኛል።

ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ልማት ማጎልበትና የስራ ፈጠራ ማዕከል ከሞሐስ ኮንሰልት ጋር በመተባበር ከተመራቂ ተማሪዎች እና ከአከባቢው ስራ ፈላጊ ወጣቶች  የተውጣጡ  ለ41 ስልጣኞች የ4 ወራት የግራፊክስ ዲዛይን ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል::

የስልጠናው አስተባባሪ ረ/ፕሮፈሰር ለሚ አማኑኤል እንዳሉት የስልጠናው ይዘት እና አይነት የኢንዱስትሪ የሰው ሃይል ፍላጐት ዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ የተቀረጸ ሲሆን፣  ክህሎት ያለው የሰው ሃይል ለቀጣሪ ድርጅቶች በማዘጋጀት ለስራ ፈላጊ ወጣቶች እና ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ እድል ለማመቻቸት የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጸዋል:: እንዲሁም ረ/ፕሮፈሰር ውብሸት ማሞ ከስራ እድል ጋር  አያይዘው ይህ ስልጠና ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ከተመረቁበት መደበኛ ዲግሪ ፕሮግራም በተጨማሪ የ4 ወር የቅያስ ግራፊክስ ዲዛይን  ክህሎት ስልጠና መውሰዳቸው በወቅቱ በስራ ገበያው ተፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችንና ከቴክኒካል ስልጠናው በተጨማሪ የSoft skill እና Employability መሰልጠናቸው  በቀጣሪ ድርጅቶች ተፈላጊ እንዲሆኑ እንደሚያስቻል እና ከስልጠናው በተጨማሪ የስራ ዕድል መመቻቸቱ ለሠልጣኞች ጥሩ ዕድል እንደሆነ ገልጸዋል::

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *