የአዲስ አበባ 2019 TVT የሥራ ዓውደ-ርዕይ በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ!

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ15 የቴክኒክና ሙያ (TVT) ኮሌጆች ተመራቂ ሰልጣኞች ያዘጋጀውን ባለ 2-ቀን ታላቅ የሥራ ዓውደ-ርዕይ ከመስከረም 26 – 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በስኬት አጠናቋል።



​ከ100 በላይ ታዋቂ ቀጣሪ ድርጅቶች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ Mohas Jobs የዝግጅቱ ይፋዊ አጋር (Official Partner) በመሆን፦


✅ ለ1,600+ ተመራቂ ሰልጣኞች “የሥራ ዝግጁነት እና የማህበራዊ ክህሎቶች” (Job readiness & Soft skills) ስልጠና በመስጠት፤
✅ ቀጣሪ ድርጅቶችን ወደ ዓውደ-ርዕዩ በመጋበዝና በማስተባበር፤
✅ የዝግጅቱን ቅድመ-ተግባራት በማሳለጥና የታቀደለትን ዓላማ እንዲመታ በማድረግ፤
✅ በቀጣሪ ድርጅቶች እና በተመራቂ ሰልጣኞች መካከል ውጤታማ የሥራ ትስስር እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።



​ለዚህ ታላቅ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉት ለአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ለቀጣሪ ድርጅቶች፣ የኮሌጅ አሰልጣኞች እንዲሁም ለተሳተፉ ተመራቂዎች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!



​”የነገውን ብሩህ የሥራ ዓለም ጉዞ በጋራ እንጀምር!”

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *