የሞሀስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ Bereketeab Yohannes በአዲስ አበባ TVT የስራ አውደ ርዕይ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር :-

ዛሬ በቀን መቁጠሪያ ላይ ያለ ተራ ቀን አይደለም። ይህ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ መሪዎችና በኮሌጆች አምራሮች በጥንቃቄ የታቀደ፣ ከየኮለጆቻችን ክህሎትን የተላበሱትን ዕንቁ ሰልጣኞቻችን ፤ተባባሪ ኢንዱስትሪዎችንና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላትን በአንድ ላይ ለአንድ አላማ ያሰባሰበ ታላቅ መድረክ ነዉ፡፡ዛሬ በዋናነት እዚህ የተሰበሰብነው ሁለት ወሳኝ አካላት ማለትም የቴክኒክና ሙያ ምሩቃነና ቀጣሪ ድርጅቶች ፊት ለፊት እንዲገናኙ ለማድርግ ነው። ዛሬ ይህ መድረክ አእንዲህ ባማርና በደመቀ መልኩ እንዲሳካ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮና ኮሌጆች የአንበሳዉን ደርሻ የተወጡ ሲሆንየሞሀስ ጆብስም የፕሮግራሙ ብቸኛ አጋር አዝጋጅ በመሆን ለፕሮግራሙ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጥኦ አድረጊዋል
Mohas Jobs በአጠቃላይ የስራገበያ ትስስርን ለማዘመን፣ በተለይም የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎችን ከአሰሪ ድርጅቶች ጋር በቀጥታ ለማገናኘት እየሰራ የሚገኝ mohasjobs.com platform ያለው ብቁ የስራ አጋር ነው። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ቢሮም ጋር ዋና ተባባሪ አጋር ሆኖ የ2018 በጀት ዓመት የቴክኒክና ሙያ ተመራቂዎችን የስራ አውደ ርዕይ ለማሳካት ሰፊ ዝግጅት አድርጓል። ከዚህም አውደ ርዕይ በፊት ሞሀስ ጆብስ ከአዲስ አበባ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር፣ ለ1600 በላይ በዘንድሮ አመት ለምመረቁ ተመራቂዎች የሥራ ዝግጁነትን እና የሙያ አስተዳደር ክህሎት ሥልጠና በመስጠት አሰልጥኗል። በዚህም ተመራቂዎች በእውቀታቸው እንዲተማመኑና በአሰሪዎች ፊት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አድርጓል። በተጨማሪም ከ430 በላይ ቀጣሪ ድርጅቶችን በማጥናትና፣ እስከ 100 የሚደርሱ ኩባንያዎችን ወደ ስራ አውደ ርዕዩ ጠርቶ አስተናግዷል።
እናንተ ተመራቂዎች፣ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች እና ኩባኒያዎች ጋር ትስስር የምትፈጥሩበት፣ ስለ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች፣ የሥራ ቦታ ባህሎች እና የሙያ መንገዶች ግንዛቤ የምታገኙበት ቦታ ነው። በመስካችሁ ውስጥ ስላሉ የተለያዩ ሚናዎች እንድታስቡ ያግዛችኋል፤ ፍላጎታችሁም በየትኛው ቦታ እንደሆነ እንድትወስኑ ይረዳችኋል። ሙያችሁን ለማቅረብ፣ አሰሪዎች የሚፈልጉትን መረጃ ለመስጠት፣ እና ያዳበራችሁትን የክህሎት ስብስብ ለማሳየት ተመራጭ ቦታ ነው ተጠቀሙበት።
እናንተ የተከበራችሁ አሰሪዎች፣ ይህ ወርቃማ ዕድል ነው። ዛረ እናንተ የምትገናኙት የስራ ፈላጊዎችን ብቻ አይደለም፤ ኩባንያዎቻችሁን ወደ ወደፊት የሚያራምድ አዲስ የታመቀ ክህሎትን ነው። ተነሳሽነት ያላቸውን፣ ክህሎት ያላቸውን ወጣቶች በቀጥታ የምትገናኙበት፣ የሥራ ቦታ ቡድኖቻችሁን በአዲሱ ትውልድ ጉልበት እና ፈጠራ የምትገነቡበት ዕድል አላችሁ።
እንዲህ ያለ መጠን ያለው ዝግጅት በአጋጣሚ አይመጣም። የጋራ ራዕይ እና የማይታክት ቁርጠኝነት ውጤት ነው። ለዚህም የስራ አውደ ርዕይ በስከት መዘጋጀት፤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ያለኝን ጥልቅና ከልብ የሚመነጭ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። እናንተ ይህን ዝግጅት የቀየሳችሁት ባለራዕዮች፣ ይህን መድረክ የነደፋችሁት አርክቴክቶች፣ እና ከሃሳብ ወደዚህ አስደናቂ እውነታ እንዲቀየር በትጋት የሰራችሁት መሃንዲሶች ናችሁ። ከመጀመሪያው የሃሳብ ብልጭታ አንስቶ እስከዚህ በዕድል የተሞላ ክፍል ድረስ፣ ወጣቶችን ለማብቃት ያደረጋችሁት የማያቋርጥ ጥረትና ዝግጅት በእውነት የሚደነቅ ነው።
በተጨማሪም፣ ለሁሉም የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች አምራሮችና አስልጣኞች ላሳያችሁት የማይናወጥ እና ዋጋ ያለው ድጋፍ ጥልቅ አድናቆቴን መግለጽ እፈልጋለሁ። እናንተ ክህሎት የሚፈጠርበት ምድጃ ናችሁ፤ እነዚህን ተመራቂዎች በእውቀት ብቻ ሳይሆን ለመሳካት በሚያስፈልግ ጽናትና ክህሎት አዘጋጅታችኋል። ለዚህ የስራ አውደ ርዕይ መሳካት ቁርጠኝነታችሁ፤ የዚህ ሙሉ ተነሳሽነት መሠረት ነው።
እና ለሞሀስ ጆብስ ሰራተኞች ፤ይህ ዝግጅት ግቡን እንዲደርስ ለሰራችሁት አስደናቂ ስራ ከልበ ላመሰግኛችሁ እወዳለወ። ጥረታችሁ የትብብር ኃይል እውነተኛ ማሳያ ነው።
ለተመራቂዎቻችን፡ ዛሬ እናንተ የስራ ፈላጊዎች ብቻ አይደላችሁም፤ የኢኮኖሚያችን ሞተሮች፣ የነገ ፈጣሪዎች፣ እና የአዲሲቷ አዲስ አበባ መሪዎች ናችሁ። በራስ መተማመን ይኑራችሁ። ደፋሮች ሁኑ። ራሳችሁን አስተዋውቁ፣ ታሪካችሁን አካፍሉ፣ እና ይህን ጊዜ ያዙ። የወደፊት ሕይወት የምትጠብቁት ነገር አይደለም፤ የምትገነቡት ነገር ነው። ግንባታውን ዛሬ ጀምሩ።
በመጨረሻም ለአጋር ድርጅቶች በተለይም ኬፕለር ኢትዮጵያና መሰል ድርጅቶች ሰልጣኞችንና ተምራቂዎችን ለማብቃት ላደርጋችሁት ጥረት ሁሉ የላቀ ምስጋናየን አእያቀረብኩ የሁለት ቀኑ መድረክ የተሳካ እንዲሆን ሁላችንም አእንድንተባብር ጥሪየን አስተላልፋልሁ፡፡
አመሰግናለሁ!

